ትውልድ ይማር!

የሠላምና ዕድገት ተልዕኮ አመራሮችና አባላት “ትውልድ ይማር!” በሚል መሪ ሃሳብ፣ በ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለ7,500 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ እንዲሁም ለ105 ሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በማበርከት ለትውልዱ ትምህርትና ለተማሪዎች የሚኖረውን አለኝታ በተግባር አሳይቷል።

ትምህርት የአንድ ሀገር የነገ ተስፋን የሚገነባ መሠረት ነው። ስለሆነም ተማሪዎች በተሟላ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚደረግ ማንኛውም ድጋፍ ለትውልድ ግንባታ የሚደረግ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ነው።

የሠላምና ዕድገት ተልዕኮ ከትምህርት ድጋፍ በተጨማሪ በተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍና የበጎ አድራጎት ሥራዎች በመሳተፍ ለወገኖቻችን ያለውን ጽኑ ፍቅርና አለኝታነት በተግባር እየገለጸ ይገኛል።

በዚህ በጎ ተግባር ውስጥ በጊዜያችሁ፣ በሀብታችሁ፣ በእውቀታችሁና በጉልበታችሁ ለተሳተፋችሁ አመራሮች፣ አባላትና ሁሉም የበጎ ተግባሩ አጋሮች ከልብ የመነጨ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የጀመርነው የበጎ አድራጎትና የሰብዓዊ ድጋፍ ተግባር በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል። በጋራ በመቆም፣ በመደጋገፍና በመረዳዳት የተሻለ ትውልድና የተሻለ ሀገር መገንባት ይቻላል።

የሠላምና ዕድገት ተልዕኮ ለሁሉም ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራንና ለመላው የትምህርት ማኅበረሰብ የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተሳካ፣ የዕውቀት፣ የስኬትና የተስፋ ዘመን እንዲሆን ይመኛል።

ትውልድ ይማር፤ ተስፋ ይበራ!
በትምህርት የነገን ሀገር እንገንባ!

Dhaloonni haa baratu

Building a better future through peace, education, and community empowerment.

Quick Links

LIVE LOCATION

© 2026 Peace & Development Mission. All rights reserved.

Scroll to Top